መነሻ ሁሉም ኮርሶችቋንቋዎች English ይመዝገቡ →
ፓኬጅ

Video Editing + DaVinci Resolve
ፓኬጅ

በአዲስ አበባ አብዛኛው Editing ስራ በPremiere Pro ይቆረጣል፤ ውድ መስሎ የሚታየው ስራ ደግሞ በDaVinci Resolve Color Grade ተደርጓል። ይህ ፓኬጅ ለእያንዳንዱ አንድ ወር ይሰጣል — Premiere ለፍጥነትና ለደንበኛ ስራ፣ Resolve ለሲኒማዊ Color።

2 ወር · 15,000 ብር 2 Certificates
ቀጣይ ክፍል · Next Batchበየሁለት ሳምንቱ · አዲስ ዙርበየሁለት ሳምንቱ አዲስ ዙር ይጀምራል — በእያንዳንዱ ክፍል የተወሰኑ ቦታዎች · ሜክሲኮ እና ሲኤምሲ ሚካኤል
አሁን ይመዝገቡ · Register →
ከጀማሪ እስከ Professional አዲስ አበባ Certificate ያካትታል Read in English → All courses in English →
Digital Marketing + Video Editing ፓኬጅ — Klick Film & Design School፣ አዲስ አበባፓኬጅ · ሁለቱም Editing Rooms

ይህ ፓኬጅ ምንድን ነው?

Video Editing + DaVinci Resolve ፓኬጅ ሁለት ሙሉ ኮርሶችን በአንድ ምዝገባ የሚያጣምር የ2 ወር ፕሮግራም ነው፦ የ1 ወር Video Editing (Premiere Pro) እና የ1 ወር DaVinci Resolve። ለሁለቱም ቅድመ ልምድ አያስፈልግም።

Cut የሚያቀርብ Editor እና ሙሉ ፊልም የሚያስረክብ Editor የሚለያዩት እዚህ ላይ ነው። Premiere Industry-ው አብሮ የሚሰራበት ነው፤ Resolve ደግሞ Grade የሚደረግበት። ሁለቱንም ማወቅ ማለት ከFootage እስከ Graded Master ድረስ ስራውን ለማንም ሳያስረክቡ መጨረስ ማለት ነው።

ለየብቻ ሲወሰዱ ሁለቱ ኮርሶች 5,000 እና 10,000 ብር — በድምሩ 15,000 ብር ናቸው፤ ፓኬጁም 15,000 ብር ነው። ልዩነቱ በተከታታይ፣ በአንድ ፕሮግራም መሰጠቱ ነው።

ምን ይማራሉ?

ፓኬጁን ሲያጠናቅቁ Professional Video Edit ማድረግ፣ Color Grade እና Sound ዲዛይን መስራት፣ እንዲሁም በAfter Effects Broadcast-quality Motion Graphics ፈጥረው በEdit-ዎ ውስጥ ማካተት ይችላሉ።

Adobe Premiere Pro Timeline Editing Story Cutting Multicam Motion Titles Audio Mixing Node-based Grading Primary እና Secondary Color Shot Matching Scopes እና LUTs Fairlight Audio Fusion Titles Delivery እና Codecs

Software እና Tools

Editors እና Colorists በሚጠቀሙባቸው Software ይሰለጥናሉ፦

Adobe Premiere Pro DaVinci Resolve Studio Fusion Fairlight Adobe Audition Media Encoder

የፓኬጁ ይዘት — 2 ወር

ወርክፍልየሚሸፈኑ ርዕሶች
ወር 1Video Editing (Premiere Pro)Editing Foundations፣ ለታሪክ መቁረጥ፣ Trimming እና Pacing፣ Multicam፣ በLumetri Color እና በAudition Sound፣ Titles፣ Export
ወር 2DaVinci ResolveResolve Pages እና Editing፣ Color Page በጥልቀት — Nodes፣ Primaries እና Secondaries፣ Scopes፣ Shot Matching፣ Power Windows፣ LUTs፤ Fairlight Sound እና Fusion Titles

የእያንዳንዱ ኮርስ ሙሉ ዝርዝር፦ Video Editing · DaVinci Resolve

ከኮርሱ በኋላ ምን መስራት ይችላሉ?

  • ሙሉ Production-ን በPremiere Pro ለብቻዎ Edit ማድረግ
  • በDaVinci Resolve Nodes Color Grade ማድረግ — Primaries፣ Secondaries እና Looks
  • በአንድ Scene ውስጥ Shots-ን አመሳስሎ አንድ ወጥ ስራ መፍጠር
  • Scopes አንብቦ Exposure እና White Balance ማስተካከል
  • Dialogue፣ Music እና Sound Effects Mix ማድረግ
  • Edit-ንም Grade-ንም የሚያሳይ Showreel መገንባት
  • ለደንበኛ ከFootage እስከ Graded Master ሙሉ ስራ ማስረከብ

የክፍል ፈረቃዎች

ሁሉም ፈረቃዎች በሳምንት 3 ጊዜ፣ በእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ለ2 ሰዓት ይገናኛሉ። በሳምንቱ ቀናት ከስምንት የቀን ፈረቃዎች፣ ወይም ከቅዳሜና እሁድ ክፍሎች ይምረጡ።

ሰኞ · ረቡዕ · ዓርብ
የሳምንት ቀናት
2 ሰዓት በክፍለ ጊዜ
ማክሰኞ · ሐሙስ · ቅዳሜ
የሳምንት ቀናት
2 ሰዓት በክፍለ ጊዜ
ቅዳሜ / እሁድ
የሳምንት መጨረሻ
የሙሉ ቀን ክፍለ ጊዜዎች

የሚፈልጉት ሰዓት ክፍት መሆኑን ለማረጋገጥ በ WhatsApp ያነጋግሩን። አዲስ ዙር በየሁለት ሳምንቱ ይጀምራል።

ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች

ፓኬጁ ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?
2 ወር። በሳምንት 3 ጊዜ፣ እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ 2 ሰዓት። ወር 1 Premiere Pro፣ ወር 2 DaVinci Resolve።
ኮርሱ ስንት ያስከፍላል?
ፓኬጁ 15,000 ብር ነው — ይህ ሁለቱን ኮርሶች ለየብቻ ከመውሰድ ጋር እኩል ክፍያ ነው (5,000 እና 10,000 ብር)። ሙሉ ወይም በክፍል መክፈል ይቻላል።
ቅድመ ልምድ ያስፈልገኛል?
አያስፈልግም። ሁለቱም ወራት ከSoftware-ው መሰረት ይጀምራሉ። Premiere አስቀድሞ መማር የResolve ወር ወደ Color Grading የበለጠ ጊዜ እንዲሰጥ ያደርጋል።
አንዱን ብቻ ብወስድ የቱን ልማር?
በአዲስ አበባ ሰፊ የEditing ስራ ከፈለጉ Premiere Pro፤ Color Grading ከፈለጉ DaVinci Resolve — ጥቂት ሰዎች የሚችሉት ስለሆነ ክፍያውም ይበልጣል። ዝርዝሩን DaVinci Resolve vs Premiere Pro ይመልከቱ።
ጠንካራ Laptop ያስፈልገኛል?
ለክፍል አያስፈልግም — በሁለቱም ቅርንጫፎች Workstations አሉ። Resolve ከባድ ስለሆነ በቤት ለመለማመድ Dedicated Graphics Card እና ቢያንስ 8GB Memory ይረዳል።
ስንት Certificates አገኛለሁ?
ሁለት — ለእያንዳንዱ ኮርስ አንድ።

ይህንን ፓኬጅ ለምን Klick ላይ?

Klick Film & Design School በአንድ ዓመት ውስጥ ከ2,000 በላይ ተማሪዎችን ያሰለጠነ፣ በአዲስ አበባ የሚገኝ የፈጠራ ስልጠና ተቋም ነው። ትምህርት ቤቱ በአንድ አድራሻ Klick Studios የተባለ Production ስቱዲዮም ስለሆነ፣ ተማሪዎች ከእውነተኛ የንግድ ስራ ጋር ጎን ለጎን ይማራሉ። ክፍሎች በሜክሲኮ እና በሲኤምሲ ሚካኤል ቅርንጫፎች በሳምንቱ ቀናትና በቅዳሜና እሁድ ይሰጣሉ።